Sunday, December 16, 2012

ብላክ ቤሪ ነጻ የንግግር መሣሪያን በመጠቀም የስልክ ጥሪ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

የብላክ  ቤሪ  የሞባይል  አይነት  ይህንን ቴክኖሎጂ  መጠቀም  የቻለው ነጻ   በሆነውን የገመድ  አልባ  የኢንተርኔት  ግንኙነት አማካኝነት  አዲስ ስፍትዌርን   በመጠቀም  ደንበኞች  ነጻ ጥሪ   እንዲያደርጉ በማስቻል  እንደሆነ  አምራች  ድርጅቱ ይፋ  አድርጓል ፡፡

ሪሰርች ኢን ሞሽን   የተሰኘው  ይህ  ኩባንያ   የብላክ ቤሪ   መልዕክት  ማስተላለፊያ ፕሮግራምን በመጠቀም  ጸሑፍ መልዕክቶችን  ከማስተላለፍ  በተጨማሪ   በነጻ  ጥሪ  ማድረግ  የሚያስችል  ቴክኖሎጂ ነው ፡፡
ተጠቃሚዎች  ይህን  ጥሪ  ማድረግ  የሚችሉት   የሚደውለውም  የሚደወልለት  ወገንም   ሶፍትዌሩን   የጫኑ  ከሆነ ሲሆን  ኩባንያው   አስር  አይነት  የኦፕሬቲን ሲስተም  ያላቸውን   የሞባይል  ቀፎዎችን ይፋ  ለማድረግ  በዝግጅት ላይ  ይገኛል ፡፡
የብላክ  ቤሪ  አስር የተለያዩ   ሲስተሞች  ያሏቸውን  ቀፎዎች እኤአ   በጥር  30  2012 ላይ ይፋ  እንደሚያደርግ የገለጸው   ኩባንያው   የመጀመሪያው   አይነት የሞባይል  ቀፎ ከወር  በኋላ   ሥራ  ላይ  እንደሚውል  ገልጿል ፡፡
በአሁኑ  ወቅት ለብላክ  ቤሪ የሞባይል ተጠቃሚዎች  ትሪንግልሚንና  የሞባይል ድምፅ   መጠቀሚያ ፕሮግራም  እየተላከ  በመሆኑ  ነጻ  ጥሪ  ለማድረግ  ጊዜው  ሩቅ እንደማይሆን  ተገልጿል ፡፡
የአዲሱ  የቴክኖሎጂ  ተጠቃሚዎች   የጽሑፍ  መልዕክት  እየተለዋወጡ  ባለቡበት  በተመሳሳይ  ሰአት  ነጻ   የስልክ ጥሪ  ማድረግ  የሚያስችላቸው  በመሆኑ  ቴክኖሎጂው  በአይነቱ   ለየት  ያደርገዋል ፡፡ 

የብላክ  ቤሪ  አምራች  ኩባንያ   እንደዚህ   አይነት  ቴክኖሎጂዎችን   ተግባራዊ ማድረጉ  ቁጥር አንድ   የሞባይል  ኩባንያ  ለመሆን ካለው  አላማ  ሲሆን   ተፎካካሪ  ኩባንያዎች  ግን  በቀላሉ  እጃቸውን  ይሰጣሉ  ተብሎ  አይገመትም ፡፡
ክርስቲያን   ቲር   በበኩሉ  በሰጠው   አስተያየት     በሞባይ  ኩባንያዎች  መካከል ያለው  ውድድር   ቀላል  እንደማይባል  በመጥቀስ   የብላክ ቤሪ  ሞባይል  አምራች  ትኩረት  ሰጥቶ  እንደሚሰራ  ገልጿል ፡፡
በአለም  የሞባይል   ገበያ  ላይ    ሳምሰንግ  22.9  በመቶ ሲይዝ  ኖኪያ   19.2  በመቶ   ድርሻ  አለው  የአፕል  ኩባንያ  ደግሞ  የ5.5  የገበያ ድርሻ  አለው ፡፡

No comments:

Post a Comment