ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ለሚዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር የብድር ስምምነት የአፍሪካ ልማት ባንክና ኬንያ ተፈራረሙ
አዲስ አበባ - የአፍሪካ ልማት ባንክና የኬንያ መንግሥት ለሁለት ፕሮጀክቶች የ158 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ እንደገለጸው ባንኩ ከኬንያ ጋር የተፈራረመው የ115 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ስምምነት ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ለሚዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት የሚውል ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር 500 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸከም ሲሆን 1 ሺህ 68 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ኃይል መስመሩ ከኢትዮጵያ የወላይታ ሶዶ ከተማ እስከ ኬንያ ሱስዋ ከተማ ድረስ የሚዘረጋ ነው፡፡
ሁለተኛው የብድር ስምምነት 43 ሚሊዮን ዶላር ያህል ሲሆን፤ በኬንያ የኢንጂነሪንግ ፋክልቲን ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑን ባንኩ ገልጿል፡፡
የብድር ስምምነቱን የተፈራረሙት የአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ገብርኤል ንጋቱ እና የኬንያ የገንዘብ ሚኒስትር ሮቢንሰን ጊቴ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

No comments:
Post a Comment