| የማዕድን ሚኒስቴር ኢዛና ማይኒንግ ዴቨሎፕመንት ከተባለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር ከፍተኛ ደረጃ የወርቅ ማዕድን ማምረት ስምምነት ዛሬ ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱ ከ22 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለማምረት የሚያስችል ነው፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት የማዕድን ሚኒስትር ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉና የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አትክልት አርአያ ናቸው፡፡ በስምምነቱ ላይ እንደተገለጸው ኩባንያው ቀደም ሲል የወርቅነና የቤዝ ሜታልስ የፍለጋና የምርመራ ፈቃድ ወስዶ በስራው ውጤታማ በመሆኑ ወደ ማዕድን ማምረት ተሸጋግሯል፡፡ ኩባንያው የፍለጋና የምርመራ ፈቃዱን ያገኘው በትግራይ ክልል በምዕራብ ትግራይ ዞን ፅምብላ ወረዳ በ51 ሺህ 200 ካሬ ሜትር ቦታ ነው፡፡ በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው በ393 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 22 ሺህ 17 ኪሎ ግራም ለማምረት አቅዷል፡፡ በዚህም ለ106 ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል፡፡ ማዕድን የማምረት ሂደት ለአካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግን የሚጠይቅ በመሆኑ ኩባንያው በሥራው ወቅትም ሆነ ሥራውን ጨርሶ በሚያቆምበት ጊዜ ለአካባቢው ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል፡፡ የማዕድን ሚኒስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት እንደተናገሩት ሚኒስቴሩ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ሃብቱን የውጭ ምንዛሪ አስተዋጽኦ በ10 እጥፍ ለማሳደግና ለኢንዱስትሪ ልማት የጀርባ አጥንት እንዲሆን የማድረግ ራዕይ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴሩ እስካሁን 135 ለሚሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገር አልሚ ባለሃብቶች 250 ፍቃዶችን ሰጥቶ በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ፈቃዶች ውስጥ 195 የማዕድን ምርመራ ፍቃድ ሲሆን 55ቱ ደግሞ የማዕድን ማምረት ፍቃዶች ናቸው፡፡ ከኩባንያዎቹ ውስጥ 66ቱ የውጭ፣ 33ቱ የሽርክና ሲሆኑ 36ቱ የአገር ውስጥ ናቸው፡፡ እንደ ወይዘሮ ስንቀነሽ ገለጻ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በአገሪቱ በማዕድንም ሆነ በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች በስፋት መሳተፋቸው ለአገሪቱ ልማት መፋጠን ትልቅ ድርሻ ስላለው የአገሪቱ ባለሃብቶ ሊበረታቱና ሊነቃቁ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ የበርካታ የማዕድን ዓይነቶች ባለቤት እንደሆነች ጥናቶች ቢያረጋግጡም ካላት የማዕድን ሃብት አንጻር ሲታይ ከማዕድን ሃብት ተጠቃሚ ለመሆን ብዙ ሊሰራበት ይገባል፡፡ በተለይም የወርቅ ማዕድንን በተመለከተ ከረጅም ዓመታት በፊት ጀምሮ ከባህላዊ አመራረት ባለፈ በዘመናዊ መንገድ በከፍተኛ ደረጃ ማምረት የተጀመረው በጣም አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ወይዘሮ ስንቅነሽ እንዳሉት ኢዛና የተባለው ኩባንያ ከፍተኛ ደረጃ የወርቅ ማዕድን ለማምረት የጥናት ስራውን በስኬት አጠናቆ የምርት ስምምነቱን ሲፈራረም በአገሪቱ ወርቅን በከፍተኛ ደረጃ በማምረት ታሪክ ውስጥ ሁለተኛው ኩባንያ ይሆናል፡፡ አገር በቀል ኩባንያ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ኩባንያው በተፋጠነ ጊዜ ውስጥ ወደ ምርት መግባት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ የኢዛና ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አትክልት አርአያ እንደገለጹት ኩባንያው ከ1986 ጀምሮ ባካሄደው ምርመራ በ1991 በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ጦረር በተባለው ቦታ በዓይነቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ፣ የብር፣ መዳብ፣ ዚንክና ሊድ ክምችት አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን አስገደ ፅምብላ ወረዳ ልዩ ስሙ ሜሊ በተባለ ቦታም የወርቅ ክምችት ማግኘቱንም ይፋ አድርገዋል፡፡ ኩባንያው ወደ ወርቅ ማምረት መሸጋገሩ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ከማስገባቱም በላይ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡ ኩባንያው የራሱ "የአናሊቲካል" ቤተሙከራ እንዳለውና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ የአክሬዲቴሽን ቢሮ የአክሬዲቴሽን ሰርተፊኬት በማግኘት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የቤተሙከራው መከፈት አገሪቱ ናሙናዎችን ወደ ውጭ በመላክ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ከማዳኑም በላይ የውጭ ምንዛሪ ለማስገባት ያስችላል ብለዋል፡፡ ኩባንያው ላለፉት 20 ዓመታት በአብዛኛው የማዕድን ጥናት ባልተካሄደባቸው ሰሜናዊ የአገሪቱ አካበባዎች የማዕድን ምርመራ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር ከህዳር 2004 ጀምሮ አዳዲስ የማዕድን ፍለጋና ልማት ጥያቄዎች መቀበል ያቆመ ሲሆን እስካሁን የተሰጡትን ከ250 በላይ ፈቃዶች ተጣርተው እስኪያልቁ ስራ |
|
No comments:
Post a Comment