Fun


ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በ90 ቀናት ውስጥ ለመገንባት



በዓለማችን የቴክኖሎጂ ውጤቶች እያደጉ በመምጣታቸው ነገሮችን በቀላሉ ማከናወን እየተቻለ ነው። የግንባታው መስክ የቴክኖሎጂ ትሩፋት ከደረሳቸው ዘርፎች መካከል የሚመደብ ሲሆን፤ ውብና ማራኪ የሆኑ ሕንፃዎች በሚያስገርም ሁኔታ በቀላሉና በአጭር ጊዜ እየተሠሩ ነው። ዊርድ ኤሽያን ኒውስም በድረ ገጹ ያስነበበው ይሄንኑ ነው።
በቻይና ውስጥ ባለ 30 ፎቅ ሆቴል በ15 ቀናት ውስጥ ተገንብቶ በማለቁ በክብረወሰን እንዲመዘገብ አድርጐታል። አሁንም ቻይና በ90 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ እ..አ በማርች ወር 1913 ለመገንባት ዕቅድ ይዛለች። የሕንፃው ቁመት 2ሺ 749 ጫማ ሲሆን፤ 220 ፎቆች ይኖሩታል። «ስካይሲቲ» የሚል መጠሪያም ተሰጥቶታል።
ሰማይ ጠቀሱ ሕንፃ የሚገነባው ቻንጋሻ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ዥያንግጃንግ ወንዝ አጠገብ ነው። 83 ከመቶ የሚሆነው የሕንፃው ክፍል አገልግሎት የሚሰጠው ለመኖሪያ ቤትነት ሲሆን ሀብታምንም ሆነ ዝቅተኛ የገንዘብ አቅም ያላቸውየኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታስቦ የተሠራ ነው። ቀሪው የሕንፃው ክፍሎች ለቢሮ፣ ለሱቅ፣ ለሬስቶራንት ወዘተ የሚያገለግሉ ናቸው። ሕንፃው እስከ ነጥብ ዜሮ ማግኒቲዩድ ድረስ ያለውን የመሬት መንቀጥቀጥ እንዲቋቋምና በድንገት የእሳት አደጋ ቢከሰት ለመጀመሪያዎቹ ሰዓታት ያህል አደጋውን መቋቋም እንዲችል ተደርጐ የሚሠራ ነው።

No comments:

Post a Comment