Friday, June 14, 2013

ኢትዮ- ቻይና ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ ምእራፍ ለማሸጋገር ተስማሙ

ኢትዮ- ቻይና ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ ምእራፍ ለማሸጋገር ተስማሙ
የቻይናው ፕሬዚዳንት ጂንፒንግ  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር የኢትዮ- ቻይና ግንኙነትን ወደ አዲስ ምእራፍ ለማሸጋገር ተስማሙ፡፡
የቻይናው ፕሬዚዳንት ጂንፒንግ  የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ቻይና በኢንዱስትሪ፣ ሰውሀይል ልማትና መሰረተልማት ማስፋፋት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ  ለመስራትና ድጋፍ ለማደረግ እንደምትሰራ ፕሬዘዳንቱ አረጋግጠዋል፡፡
እንዲሁም ዕውነተኛ የቻይና አጋር ከሆነችው አፍሪካ ያለው አጋርነት ለማጎልበት ሀገራቸው እንደምትሰራ ያረጋገጠት የቻይናው ፕሬዚዳንት ጂንፒንግ በመሆኑም ቻይና ለአፍሪካ የምታደርገው የሰላም፣ ልማትና ትብብር ድጋፍን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡ የአፍሪካና ቻይና ግንኙነቱም  ሁለቱን  ወገኖች  እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በሁሉም መስክ ግንኙነቷን  ለማሳደግና በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ  ለሚፈልጉ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች  ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል ፡፡
ኢትዮጵያና ቻይና ለትብብር ታላቅ እምቅ አቅም ያላቸው ሃገሮች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ለዚህም ሁለቱ ሃገራት ምጣኔ ሃብታቸውን ለማሳደግና የዜጎቻቸውን ህይወት ለመለወጥ ተግተው እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ በባቡርና ሀይል ማመንጫ ግንባታ እየተሳተፉ ያሉ ኩባንያዎች በተቀመጠላቸው ቀነ ገደብ ስራቸውን ጨርሰው እንደሚያስረከቡ አረጋግጠዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያመ ደሳለኝ በቤጀነግ ያነጋገሩአቸው የኩባንያ ሃላፊዎች ሰፊ የሆነ መዋእለንዋይና የሰው ሃይል በማሰማራት በ 5 አመቱ ዕቅድ ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቶቻችን ለማጠናቀቅ ሁኔታዎችን እያመቻቹ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
እነዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዝን ቢያንግ ጋርም በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡
በተለይም በቀጣይነት የሁለቱ ሀገራት ፓርላማዎች በጋራ በሚሰሩበት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment