Friday, June 14, 2013

ኢትዮጵያና ቻይና በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ቻይና በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት ተስማሙ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከቻይና አቻቸው ሊን ኪንግ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለማርያም ደሳለኝ በውይይቱ እንዳሉት ቻይና ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገው ድጋፍ አጠናክራ ልትቀጥል ይገባል፡፡
ኢትዮጵያ ከቻይና በተለያዩ የልማት ዘርፎች በተለይም በባቡርና መንገድ ግንባታ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል ፡፡  
ቻይና በአፍሪካ ሰላም  ጸጥታ  ልማትና እድገት ማረጋገጥ ጉሉህ ሚና እንዳላት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህንንም በማጠናከር የቻይናና አፍሪካ ግንኙነት ለማጎልበት ኢትዮጵያ ሚናዋን እንደምትጫወት አረጋግጠዋል፡፡
የቻይና ጠቅላይ ሚኒስተር ሊን ኪንግ በበኩላቸው ቻይናና ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያቸውንና የህዝባቸውን ኑሮ ለማሻሻል በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በመሰረተልማት ፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግና  የኢንዱስትሪ ዞን ግንባታ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር መንግስታቸው በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡.
ቻይና ከኢትዮጵያ እንዱሁም ከአፍሪካ ያላትን ግንኙነት ወደ አዲስ ምእራፍ ለማሸጋገር እንደምትሰራም ጠቅላይ ሚኒስተር ሊን ኪንግ  አረጋግጠዋል ፡፡

No comments:

Post a Comment