Friday, June 14, 2013

ግድቡ በግብፅና ሱዳን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማያሳድር ደቡብ ሱዳን ገለፀች

    ግድቡ  በግብፅና ሱዳን ላይ  አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማያሳድር ደቡብ ሱዳን ገለፀች
ደቡብ ሱዳን ግብፅና ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቀረበች፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአባይ ወንዝ ተፋሰስ ላይ መገንባቱ የግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የአሁኑና ቀጣይ ትውልዶች ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን የደቡብ ሱዳን ዋና ተደራዳሪ ፔጋን አሙም ገለፁ፡፡

የግድቡ መገንባት በታችኛው የናይል ተፋሰስ ሀገራት ማለትም በግብፅና ሱዳን ላይ የሚያስከትለው ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖ አለመኖሩንም ዋና ተደራዳሪው አክለው ገልፀዋል፡፡
ግድቡን አስመልክቶ ከሰሞኑ የግብፅ ባለስልጣናት ሲሰነዝሯቸው የነበሩትን አስተያየቶች ደቡብ ሱዳን በአንክሮ ስትከታተል መሰንበቷን የጠቀሱት ዋና ተደራዳሪው የአሁኑና ቀጣይ ትውልዶቻቸው ዕጣ ፈንታ ይሰምር ዘንድ የናይል ተፋሰስ ሀገራት በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ በትብብር እንዲሰሩ መክረዋል፡፡
"ኢትዮጵያ የሌሎችን ጥቅም በማይጎዳ ሁኔታ የአባይን ውሃ ለኤሌክትሪክ ማመንጨትም ሆነ ለመስኖ አገልግሎት የመጠቀም መብት አላት፡፡ ግብፅና ኢትዮጵያም በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ብለዋል ዋና ተደራዳሪው፡፡
ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ አባል አገር እንደመሆኗ በወንዙ አጠቃቀም ዙሪያ ከፍትሃዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ ከሌሎች የተፋሰሱ አገራት ጋር በቅርበት ትሠራለችም ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ዥንዋ

No comments:

Post a Comment