ግብፅ የያዘችው አቋም ተቀባይነት የለውም
ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር በረከት ስምኦን ገለፁ፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው ግብፅ የግድቡን የሃይል ማመንጨት አቅም መቀነስ እንደመፍትሔ ማቅረቧ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር አቶ በረከት ስሞኦን ግብፅ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የግንባታ
ሂደቱ 22 ነጥብ 5 በመቶ የደረሰውና በተያዘው ዓመት 26 በመቶ ስራው እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው የህዳሴው ግድብን
አስመልክቶ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የያዙት አቋም ትክክል አለመሆኑንም ሚኒስትር በረከት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር
በረከት አያይዘው እንደገለፁት ግብፅ ጉዳዩን የውስጥ የፖለቲካ ችግሯን ለማርገብ እየተጠቀመችበት መሆኑን ጠቅሰው
ሀገሪቱ የጦርነት አማራጭ የተዘጋ አይደለም ትበል እንጂ ወደዚህ ተግባር ትገባለች ተብሎ አይጠበቅም ብለዋል፡፡
የውሃና
ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው የጦርነት አማራጭ እንደማያዋጣ የተገነዘበ የሚመስለው የግብፅ መንግስት
የህዳሴን ግድብ የማመንጨት አቅም፣ የሚይዘውን የውሃ መጠንና ከፍታ እንዲቀንስ የሚያነሳው የመፍትሔ ሃሳብ
ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ ህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር በረከት ስሞኦን እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮና በ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በህዳሴው ግድብ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ባተኮረው የቀጥታ ውይይት ላይ በአገር ውስጥና ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያሳዩት ያሉትን ግድቡን የመገንባት ቁርጠኝነትና ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሃላፊዎቹ ጥሪ አቀርበዋል፡፡
No comments:
Post a Comment