“የእድገትና ትራንስፎርሜሸን እቅድ ይሳካል” ሚኒስትር ሱፊያን
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሱፊያን አህመድ የ2006 የበጀት ረቂቅ ላይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2006 ዓ/ም በቀረበው በጀት ረቂቅ ላይ ተወያየ፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በቀረበው ማብራርያ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡
ከነዚህም በመንገድ ግንባታ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስፋፋትና በሌሎች የስራ መጓተት የሚታይባቸው ፕሮጀክቶች ላይ የሚመደበው በጀት ለብክነት እየተዳረገ አይደለም ወይ፣ በጀት ለታለመለት አላማ ስለመዋሉ እየተደረገ ያለው ከትትል ምን ይመስላል የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
ሚኒስትር ሶፍያን አህመድ በሰጡት ምላሽ ጉድለቶች ቢታዩም የሚመደበው በጀት ለታለመለት አላማ እየዋለ እንደሆነ ገልፀው በፕሮጀክት ስራዎች ላይ ትልቁ ችግራችን የማስፈፀም አቅም ውስንነት ነው ብለዋል፡፡
በ2006 በጀት ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች ለያንዳንዳቸው መቼ ተጀመረው እንደሚጠናቀቁ ፕሮግራም ተቀርፆላቸው ይሰራሉ ብለዋል፡፡
ኢኮኖምያዊ እድገቱ ባለፉት አመታት በነበረው እድገት እንደሚቀጥልና በዚህም የእድገትና ትራንስፎርሜሸን እቅዱ እንደሚሳካ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment