Thursday, October 10, 2013


Technology that could solve Power Cut in Addis Ababa

A German Company is to provide technology that could solve the country's electric power cuts.
Though there haven't been any data as to the amount of loss caused on the country's economy due to continuous power cuts, it is evident that the economy must have suffered a great deal.

It is for alleviating this problem in mind that the German's Shetwor Emergency power System company is preparing to provide a technology that would regulate the fluctuating power and even sustain power in cases of power cuts.

This technology that would be fit onto some essential services like hospitals, Hotels, Banks and Power Stations can deliver a continuous power supply for about 2 hours at times of power cuts.


Girum Tebeje
Partial Article from Ethiopian Reporter

በኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ምክንያት በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚደርሰው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ባይቀርቡም፣ በኢኮኖሚው ዋና ዋና ዘርፎች ላይ

የሚደርሰው ጉዳት ቀላል አለመሆኑ ስለሚታወቅ፣  በድንገተኛ ኃይል መቋረጥ ምክንያት የሚደርሱ ችግሮችን ለመቋቋም አንድ የጀርመን ኩባንያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሊያቀርብ መምጣቱን አስታወቀ፡፡

ሽቴውረር ኢመርጀንሲ ፓወር ሲስተምስ ኩባንያ በኢትዮጵያ በሆስፒታሎች፣ በትልልቅ ሆቴሎች፣ በባንኮችና በኃይል ማሠራጫ ጣቢያዎች ላይ ተገጥመው ድንገተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥና መዋዠቅ በሚከሰትበት ወቅት፣ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ኃይል ለተወሰነ ጊዜ እንደነበረው ሳይቋረጥ እንዲቀጥል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይዞ መምጣቱን አስታውቋል፡፡

ኩባንያው ምርቶቹን በኢትጵያ ለማቅረብ ከመምጣቱም በላይ የጥገናና የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጥ ቡድንም በአዲስ አበባ እንደሚከፍት ገልጿል፡፡ የኩባንያው ዋና ኃላፊ ሚስተር ስቴፈን ሬዲ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ከሁለት ሰዓት ተኩል በላይ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ የድንገተኛ ኃይል መቋረጥ ችግሮች መከላከያ (ዩፒኤስ) ጨምሮ፣ ለሆስፒታሎች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት የሚሰጡ፣ ኤሌክትሪክ ሲጠፋ ተክተው የሚበሩና በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ መገልገያዎችን ይዞ መጥቷል፡፡

የጤና ጥበቃና የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮችን ያነጋገረው ኩባንያው፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልን እንደጎበኘ አስታውቋል፡፡ በተለያዩ ሆቴሎችም ተዘዋውሮ ጥናት ማድረግ እንደጀመረም ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

ሚስተር ሬዲ ማክሰኞ ዕለት ከባንኮችና ከመድን ድርጅቶች ለተውጣጡ አካላት በሆቴል ደ ሊዮፖል በሰጡት መግለጫ፣ በኃይል መቋረጥ ምክንያት ሊጠፉና ሊሰረቁ የሚችሉ መረጃዎችን ጨምሮ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ያሉዋቸውን ቴክኖጂዎች አስተዋውቀዋል፡፡

በጀርመን የአንድ ኪሎ ዋት ሃወር የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ከስምንት እስከ 16 ዩሮ ኪሳራ ሲያስከትል፣ ለአንድ ሰዓት የኃይል መቋረጥ ደግሞ በጀርመን ኢኮኖሚ ላይ ከ600 ሚሊዮን እስከ 1.3 ቢሊዮን ዩሮ ኪሳራ ያደርሳል ተብሏል፡፡ ለአንድ ቀን ከቆየ ደግሞ ከ14 እስከ 30 ቢሊዮን ዩሮ ኪሳራ እንደሚያደርስ ጥናት ተደርጎበታል፡፡ ሆኖም በጀርመን በዓመት ለ15 ደቂቃ ብቻ የኃይል መቋረጥ እንደሚያጋጥም ሚስተር ሬዲ አስታውቀዋል፡፡
በአንፃሩ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የኃይል መቋረጥ ምን ያህል ኪሳራ ማድረሱን የሚጠቁሙ መረጃዎች ባይኖሩም፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ኃይል አቅርቦት በድንገት የሚቋረጥ በመሆኑ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment