አህመዲነጃድ ለአፍሪካ ህብረት ክብረ በአል አዲስ አበባ ይመጣሉ
የኢራኑ ፕሬዚዳንት መሀሙድ አህመዲነጃድ በ50ኛው የአፍሪካ ህብረት የምስረታ ክብረ በአል ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ይገባሉ ተባለ ፡፡
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ፥ ኢራን በህብረቱ የታዛቢነት ቦታ እንዳላትና በህብረቱ ስብሰባዎች ላይም በንቃት ስትሳተፍ መቆየቷን ተናግረዋል፡፡
ቃል አቀባዩ አያይዘውም የኢራን መንግስት ከአፍሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት አለው ነው ያሉት ፡፡የአሁኑ የፕሬዘዳንቱ የአዲስ አበባ ጉብኝትም ይህንን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል ፡
No comments:
Post a Comment