የዕውቁ አጥቂ አዳነ ግርማ ጤንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል .ክለቡ የተጨዋቹን ህክምና ወጪ ፌዴሬሽኑ ሊሸፍን ይገባል እያለ ነው
ከአዳነ
ግርማ የጤንነት መታወክ ጋር በተያያዘ ቅድስ ጊዮርጊስ የህክምናውን ወጪ በመሸፈን ላይ ቢሆንም ይህን ወጪ መሸፈን
ያለበት ፌዴሬሽኑ ነው በማለት ፌዴሬሽኑ ወጪውን እንዲሸፍን ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ቅድስ ጊዮርጊስ የዓለም አቀፉን እግር
ኳስ ማህበርን (ፊፋ) ደንብ በመጥቀስ የካቲት 25 እና መጋቢት 23/2005ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ጥያቄ
ባቀርብም ምላሽ ማግኘት ግን አልቻልኩም እያለ ነው፡፡ ‹‹ከአንድም ሁለት ጊዜ በደንቡ መሰረት እንዲፈፀምልን
ጠይቀናል ተግባራዊ ሊሆን ግን አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ምን እንደሆነ ሊገባን አልቻለም፡፡›› ሲሉ የክለቡ ስራ
አስኪያጅ አቶ ተረፈ አንበርብር ለስፖርት አዲስ ድህረ ገፅ ተናግረዋል
No comments:
Post a Comment