from:ethiopianreporter.com
በአንድ ቢሊዮን ብር አዲስ የፓርላማ ሕንፃ ሊገነባ ነው
አሁን አገልግሎት እየሰጠ ከሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኝ ቦታ ላይ አንድ ቢሊዮን ብር የሚያወጣ አዲስ የፓርላማ ሕንፃ ሊገነባ ነው፡፡
ባለፈው ማክሰኞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃንና ሌሎች የፓርላማ አባላት በተገኙበት የሕንፃውን ዲዛይን አሸናፊ የሆኑት ድርጅቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡ በዚሁም መሠረት አዲስ መብራቱ ኮንሰልቲንግ አርክቴክቶችና ኢንጂነሮች፣ ስቱዲዮ ሰቨንና ገሉክ ትራዩርኒት አርክቴክትስ የተባለው የሆላንድ ኩባንያ ተጣምረው የሠሩት የፓርላማ ሕንፃ ዲዛይን አሸናፊ መሆኑ ታውቋል፡፡
የሕንፃው ግንባታው ከዘጠኝ ወራት በኋላ ይጀመራል የተባለ ሲሆን፣ አጠቃላይ ግንባታውም ሁለት ዓመት ይፈጃል ተብሏል፡፡ በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገነባው ይህ ሕንፃ 31,463 ካሬ ሜትር ላይ እንደሚያርፍም ታውቋል፡፡
No comments:
Post a Comment