Wednesday, January 16, 2013


የፌዴሬሽኑ ሃላፊዎችና የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ መግለጫ እየሰጡ ነው. 64 ሚሊዮን ብር ለሽልማት ቀረበ


ጥር 8/2005ዓ.ም
በ29ኛው አፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የሚካፈለውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዝግጅት አሰመልክቶ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የገቢና ጉዟ ዝግጅትን አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ ስራ ሃላፊዎች በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ለሚያስመዘግበው ውጤት 64.4 ሚሊዮን ብር ለሽልማት መዘጋጀቱን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡ ቡድኑ ከምድቡ ካለፈ 8ሚሊዮን ብር፤አራት ውስጥ ከገባ 11.5 ሚሊዮን ብር፤ ለዋንጫ ከደረሰ 23ሚሊዮን ብር ፤ዋንጫ ካገኘ 46ሚሊዮን ብር እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ ይህ ሽልማት ከአሰልጣኝ ቡድኑ አባላት ውጪ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል

No comments:

Post a Comment