Thursday, November 29, 2012


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዳዲስ የመንግስት ባለስልጣናትን ሹመት አፀደቀ



ዶክተር ደብረፂዮን  ገብረሚካዔል  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
አቶ ሙክታር ከድር  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
ዶክተር ቲወድሮስ አድሃኖም  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ  የጤና  ጥበቃ ሚኒስትር
አቶ ከበደ ጫኔ  የንግድ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።
አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሆነው ይሰራሉ።
ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ እና የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመሆን ነው የተሾሙት።።
በዚህም የኢትዮጵያ  መንግስት አስቅድመው  በምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትርነትና  የትምህርት ሚኒስትርነት የተሾሙትን  አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ  ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይኖሩታል  ማለት ነው።
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ደግሞ ከጤና ጥበቃ  ሚኒስትርነታቸው ተነስተው ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት። በምትካቸው የቀድሞው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment